
ጎንደር፡ መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ላይ አርማጭሆ ወረዳ ትክል ድንጋይ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
በሰልፉ ላይ የተለያዩ መልዕክቶች የተላለፉ ሲኾን ከመልዕክቶቹ መካከልም፦
👉ግድባችን በራስ አቅም እና በአፍሪካዊነት ኩራት የተገነባ ነው።
👉የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ ማንሰራራት ምልክት ነው።
👉የሕዳሴ ግድብ የብልጽግናችን አሻራ ነው።
👉የሚደገም ድል፣ የሚጨበጥ ብስራት የሕዳሴ ግድብ የሚሉ እና መሰል መልዕክቶች በድጋፉ ሰልፉ ተላልፈዋል።
በድጋፍ ሰልፉ የወረዳው ነዋሪዎች እና የሥራ ኀላፊዎች ተሳታፊ ኾነዋል።
ዘጋቢ፦ ቃልኪዳን ኃይሌ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን