የታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቅን አስመልክቶ ሰላማዊ ሰልፍ በሰቆጣ ከተማ እየተካሄደ ነው።

27

ሰቆጣ: መስከረም 06/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የሕዳሴውን ግድብ መመረቅ አስመልክቶ ሰላማዊ የድጋፍ ሰልፍ በሰቆጣ ከተማ እየተካሄደ ነው።

ሰልፈኞቹም ዓባይ የሁላችን ነው፤ የመንግሥታችንን የልማት ዕቅዶች እንደግፋለን እና ሌሎች መፈክሮችን በመያዝ ድምጻቸውን እያሰሙ ይገኛሉ።

በሰልፉ ላይ የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን፣ የሰቆጣ ከተማ ነዋሪዎች፣ ወጣቶች፣ መምህራን እና ተማሪዎች ወጥተው እየደገፉ ነው።

ዘጋቢ፦ደጀን ታምሩ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቅን ምክንያት በማድረግ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ደስታቸውን በሰላማዊ ሰልፍ እየገለጹ ነው።
Next articleየሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ጅማሮ