
ጎንደር፡ መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቅን ምክንያት በማድረግ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ደስታቸውን በሰላማዊ ሰልፍ እየገለጹ ይገኛሉ።
ሰልፈኞቹ ከየክፍለ ከተማው የመጡ ሲኾን የተለያዩ መልዕክቶችን እያስተላለፉ ነው።
ካስተላለፏቸው መልዕክቶች መካከልም፦
👉ግድባችን የመነሳት ደወል ብሥራት የኢትዮጵያ ድምቀት
👉የውጭ ተጽዕኖ ያልበገረው ኢትዮጵያዊ አንድነት ላይ የቆመ ግድብ
👉የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ የማንሰራራት ምልክት
👉የህዳሴ ግድብ! የብልጽግናችን አሻራ
👉ግድባችን የመቻል ማሳያ የማንሰራራት ጅማሮ ምልክት
👉 የሚደገም ድል፣ የሚጨበጥ ብስራት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እና ሌሎችም መልዕክቶችን እያሰሙ ነው።
ዘጋቢ፦ ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን