
ባሕር ዳር: መስከረም 06/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ በባሕርዳር ከተማ የደስታ የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
የባሕርዳር ከተማ ነዋሪዎች ደስታቸውን በተለያዩ መልእክቶች እየገለጹ ወደ አደባባይ እየወጡ ነው።
👉 በኅብረት ችለናል
👉ግድባችን በራሳችን አቅም የገነባነው የአንድነታችን እና የአብሮነታችን መሰሶ ነው።
👉ግድባችን የፍትሕ መነጸራችን፣ የነጻነት መልእክታችን
👉 ሕዳሴ የሚደገም ድል፣ የሚጨበጥ ብስራት ነው
👉ግድባችን ለተፋሰሱ ሀገራት በረከት እንጂ ጉዳት አያመጣም
👉 ግድባችን የመነሳሳት ደወል ብሥራት፣ የኢትዮጵያ ድምቀት የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶችን በማሰማት ነው ደስታቸውን እየገለጹ የሚገኙት።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ ዛሬ በአማራ ክልል ከተሞች የድጋፍ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!