
ባሕር ዳር: መስከረም 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ቤቶች ልማት ድርጅት በአዋጅ ከተሠጠው ተግባር ውስጥ የመኖሪያ ቤቶችን ማልማት አንዱ ነው። ድርጅቱ በ2017 በጀት ዓመት በክልሉ አንዳንድ ከተሞች የመኖሪያ ቤቶችን ግንባታ እየተከናወነ መኾኑን የድርጅቱ ዋና ሥራ አሥኪያጅ አበረ ሙጬ ገልጸዋል።
በደሴ ከተማ አሥተዳደር ብቻ 48 መኖሪያ ቤቶች እና 20 የንግድ ቤቶችን ማጠናቀቅ መቻሉን በማሳያነት አንስተዋል።
ይሁን እንጂ በክልሉ በነበረው የጸጥታ እና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ምክንያት በሚፈለገው ልክ ቤቶችን ማልማት አለመቻሉን ነው ዋና ሥራ አሥኪያጁ የገለጹት።
መኖሪያ ቤቶችን ከማልማት ባለፈ
ደንበኞች የለሙ መኖሪያ ቤቶችን በባለቤትነት ስሜት ያለመጠበቅ፣ ሕጉ ባስቀመጠው የጊዜ ገደብ ያለመልቀቅ የመሳሰሉ ችግሮች እንደነበሩም ገልጸዋል።
በ2018 በጀት ዓመት የጸጥታው ሁኔታ ከተስተካከለ እና በቂ የብድር አቅርቦት ከተገኘ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ተመጣጣኝ ዋጋ ያላቸው ቤቶችን ለመሥራት መታቀዱን ገልጸዋል።
ድርጅቱ በክልሉ በሚገኙ 14 ከተሞች ያሉትን የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን መልሶ ለማልማትም ቅድመ ዝግጅት መደረጉን ገልጸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!