የአማራ ሴቶች ማኅበር ለተጋላጭ ሴቶች እና ልጃገረዶች የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።

2
ባሕር ዳር: መስከረም 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ሴቶች ማኅበር ከተባበሩት መንግሥታት የሥነ ሕዝብ ፈንድ ጋር በመተባበር በሚተገብረው ፕሮጀክት ለ90 ተጋላጭ ሴቶች እና ልጃገረዶች ድጋፍ አድርጓል።
የአማራ ሴቶች ማኅበር ዋና ዳይሬክተር ገነት ወንድሙ የአማራ ሴቶች ማኅበር በክልሉ ብሎም በኢትዮጵያ የተዛባ የሥርዓተ ጾታ አስተሳሰብ እና አላስፈላጊ ተግባራቶችን በመከላከል የሴቶችን ሁለንተናዊ መብት እና ደኅንነት ማስጠበቅ ይገባል ብለዋል።
ዳይሬክተሯ ሁሉም የክልሉ ሴቶች በየትኛውም የልማት አውታር ውስጥ ተሳታፊ እና ተጠቃሚ እዲኾኑ ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
እንደ አማራ ሴቶች ማኅበር የሚያግዙ ብዙ ፕሮጀክቶች አሉ ያሉት ዳይሬክተሯ ከእነዚህም ውስጥ የተባበሩት ሥነ ሕዝብ መንግሥታት ፈንድ ለአምስት ዓመታት አብሮ ሢሠራ ቆይቷል ብለዋል፡፡
ዛሬም ለተደራጁ ሴትች ከ750 ሺህ ብር በላይ ወጭ በማድረግ ለተጋላጭ ሴቶች እና ልጃገረዶች ታጥቦ ጥቅም ላይ የሚውል ከጨርቅ የሚሠራ የሴቶች የንጽህና መጠበቂያ ሞዴስ በማምረት እና ለገበያ በማቅረብ እራሳቸውን እንዲችሉ የማድረግ ሥራ ተሠርቷል ብለዋል፡፡
ለሥራቸው ግብዓት የሚኾን ሥልጠና ላለፉት ሦሥት ወራት ተሰጥቷቸው ለሥራ ዝግጁ መኾናቸውም ነው የተነገረው፡፡
ወደ ሥራ ለሚሠማሩት ለእነዚህ ሠልጣኞች በአጠቃላይ በ11 ነጥብ 3 ሚሊዮን ብር ወጭ የተገዙ የልብስ ስፌት እና ሌሎች ቁሳቁሶች ርክክብ እንዲሁም በቡድን ለታቀፉ 15 ሴቶች መነሻ ካፒታል 800 ሺህ ብር ድጋፍ ተደርጓል ነው ያሉ፡፡
በሥነ ሥርዓቱ ላይ የተለያዩ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
ዘጋቢ፦ ሰናይት በየነ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ሕዳሴ ግድብ የኢኮኖሚያችን ተጨባጭ አቅም ነው” ጥላሁን መሐሪ (ዶ.ር)
Next articleበጸጥታ ችግር ምክንያት በተፈለገው ልክ ቤቶችን ማልማት አለመቻሉን የአማራ ክልል ቤቶች ልማት ድርጅት ገለጸ።