ለመካከለኛ እና ዝቅተኛ መሪዎች ሥልጠና እየሰተጠ ነው።

2
ደብረማርቆስ: መስከረም 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በብልጽግና ፓርቲ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት “ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ መልዕክት በዞኑ ለሚገኙ 25 የወረዳ እና የከተማ አሥተዳደር መካከለኛ እና ዝቅተኛ መሪዎች ሥልጠና እየሰተጠ ነው፡፡
በብልጽግና ፓርቲ የምሥራቅ ጎጃም ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋየ በላይ ሥልጠናው የብልጽግና ፓርቲ ያለፉት ዓመታት ጉዞ እና የቀጣይ ዓመታት የትኩረት መስኮች ላይ ትኩረት ማድረጉን አብራርተዋል።
ኀላፊው ሥልጠናው የመሪዎችን ብቃት እና ቁርጠኝነትን በማሳደግ የተጀመሩ ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የጋራ መግባባት ላይ ለመድረስ ዓላማ ያደረገ እንደኾነም ተናግረዋል፡፡
ሥልጠናውን በደብረ ማርቆስ ከተማ ሲወስዱ አሚኮ ያገኛቸው የምሥራቅ ጎጃም ዞን የመንግሥት ሠራተኛ የፓርቲ አባላት ሥልጠናው አቅማቸውን ያሳደጉበት እና በቀጣይም ፓርቲው ለሚያከናውነው ሁለንተናዊ ተግባር የጋራ አቋም የያዙበት እንደኾነ አብራርተዋል፡፡
በደብረ ማርቆስ ከተማ የተካሄደውን ሥልጠና ሲያስተባብሩ አሚኮ ያገኛቸው የዞኑ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎችም በመድረኩ ፓርቲው ባለፉት ዓመታት ባከናወናቸው ተግባራት ላይ ግልጽነት የተፈጠረበት እና በቀጣይም ለሚከናወኑ ተግባራት የጋራ መግባባት የተፈጠረበት እንደኾነ ተናግረዋል፡፡
ፓርቲው የሕዝቡን ሁለንተናዊ ተሳትፎ በማረጋገጥ በቀጣይ በዕቅድ የተያዙ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን ለመፈጸም በሚሠራው ሥራ መሪዎች፣ አባላቱ እና ሕዝቡ የበኩላቸውን ድርሻ ሊወጡ እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እውቀትን፣ ፅናትን፣ አልሸነፍ ባይነትን እና አንድነትን ለኢትዮጵያ ሕዝብ ያስተማረ ነው”
Next articleበምዝገባ የታየው ስኬት በትምህርት ወቅት እንዲደገም ወላጆች ልጆቻቸውን ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩ ተጠየቀ።