በወልድያ ከተማ አስተዳደ ስር ባሉ 40 ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሥራ ተጀምሯል።

3
ወልድያ፡ መስከረም 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የ2018 የትምህርት ዘመን መማር ማስተማር መስከረም አምስት በወልድያ ከተማ ተጀምሯል።
በከተማ አስተዳደሩ የየጁ ገነት አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ካሳዬ በሪሁን በክረምት ወቅት ትምህርት ቤቶችን ለመማር ማስተማር ዝግጁ መደረጋቸውን ገልጸዋል። እስከ ነሀሴ መጨረሻ ተማሪዎችን መዝግበው በማጠናቀቅ መስከረም አምስት የመማር ማስተማር ሥራው ተጀምሯል ነው ያሉት።
የወልድያ አጠቃላይና ከፍተኛ ትምህርት መሰናዶ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አሻግሬ አበራ ትምህርት ቤቶችን ከማስዋብ ባሻገር የትምህርት ክፍል፣ የክፍለ ጊዜ፣ የክበባት ድልድል እና ሌሎች የትምህርት ቤት አደረጃጀቶች ቀድሞ መጠናቀቁን ነግረውናል።
ወላጆች ልጆቻቸውን በወቅቱ አስመዝግበዋል ያሉት ርእሰ መምህሩ ተማሪዎችም መስከረም አምስት የመጀመሪያ መማር ማስተማር ሂደት ተሟልተው መገኘታቸውን ገልጸዋል።
የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ትምህርት መምሪያ ኀላፊ አስራት በሪሁን በመምሪያው ስር ያሉ 40 ትምርህርት ቤቶች ሁሉም የመማር ማስተማር ሥራ መጀመራቸውን ገልጸዋል።
በክረምት ወቅት በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ትምህርትቤቶችን የማስዋብና ለመማር ማስተማር ዝግጁ ሲደረግ መቆየቱንም ነግረውናል።
ከተማው ሰላሙ የተረጋገጠ በመሆኑ የትምህርት ሂደቱን የሚያደናቅፍ ምንም ችግር እንደሌለም ኀላፊው ገልጸዋል።
አሚኮ ተንቀሳቅሶ በቃኛቸው ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማር ሂደቱ በስኬት እየተከናወነ መሆኑን ታዝበናል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleበ280 ትምህርት ቤቶች ትምህርት መጀመሩን የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር አሥታወቀ።
Next articleየታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለሁሉም የሚደርስ የንጋት ብርሃን ነው።