
ባሕር ዳር: መስከረም 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ ”እምርታ እና ማንሠራራት” በሚል መሪ መልዕክት ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር የውይይት መድረክ አካሂዷል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ እና ግድቡ ለኅብረተሰቡ ያለው ምጣኔ ሃብታዊ እና ፖለቲካዊ ጥቅም በሚል መነሻ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት ተካሄዶበታል።
የሕዳሴ ግድቡ ከጅማሮው እስከ ፍጻሜው ያጋጠሙ ችግሮች እና እንዴት ማለፍ እንደተቻለ በመድረኩ ቀርቧል። ኢትዮጵያውያን ድሮ በዓድዋ አሁንም በዳግም ዓድዋ በሕዳሴ ግድብ ግንባታ ለአፍሪካ የመቻል ምሳሌ መኾናቸው በመድረኩ ተንጸባርቋል።
አሚኮ ያነጋገራቸው ተሳታፊዎች የግድቡ በራስ አቅም እንችላለን ተብሎ የተሠራ በመኾኑ በቀጣይ ሊሠሩ የታቀዱ ታላላቅ የልማት ሥራዎችን እንዲሠሩ ተነሳሽነት የሚፈጥር መኾኑን ተናግረዋል፡፡
የአሁኑ ትውልድም ከዚህ በመማር አርቆ አሳቢና ነገሮችን በትዕግስት የሚፈጽም ሊኾን ይገባል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ፍሬሕይወት አዘዘው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!