የትምህርት ሂደቱ በታቀደው ጊዜ መጀመሩ ተገቢውን የትምህርት ሽፋን ለመስጠት ያስችላል።

2
ደባርቅ: መስከረም 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ጎንደር ዞን ላለፉት ሦሥት ሳምንታት የተማሪዎች ምዝገባ ሲካሄድ ቆይቶ የመማር ማስተማር ሥራው ዛሬ ተጀምሯል።
የሰሜን ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ምክትል ኀላፊ አጸደ በሬ እንደገለጹት የመማር ማስተማር ሥራውን የተሻለ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት መከናዎናቸውን ተናግረዋል።
የትምህርት መሠረተ ልማቶችን ማሻሻል፣ መምህራንን ማብቃት እና ተማሪዎችን በትምህርት ቁሳቁስ መደገፍ ከተከናዎኑ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መካከል እንደሚጠቀሱ አብራርተዋል።
የትምህርት የንቅናቄ መድረክ በማዘጋጀት የተለያዩ የቅስቀሳ እና የግንዛቤ ፈጠራ ሥራዎች መሥራታቸውንም አክለዋል።
አሚኮ ያነጋገራቸው የዋልያ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን እንደገለጹት አስፈላጊውን የትምህርት ቅድመ ዝግጅት በማድረግ በሥራ ገበታቸው ተገኝተው የመማር ማስተማር ሥራውን እያከናዎኑ ነው።
የትምህርት ሂደቱ በታቀደው ጊዜ መጀመሩ ተገቢውን የትምህርት ሽፋን መስጠት እንደሚያስችልም ገልጸዋል።
ተማሪዎችም በበኩላቸው አስፈላጊውን የትምህርት ቁሳቁስ በማሟላት በትምህርት ገበታቸው ተገኝተው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ እንደሚገኙም ተናግረዋል።
የትምህርት ሥራው በወቅቱ መጀመሩ ውጤታማ የመማር ማስተማር ሥራ ለመከዎን እንደሚያስችልም አብራርተዋል።
የመማር ማስተማር ሥራው በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገልጿል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየትምህርት ጊዜ ብክነትን ለማስቀረት ወላጆች ልጆቻቸውን በወቅቱ ወደ ትምህርት ቤት መላክ ይገባቸዋል።
Next articleየግድቡ መጠናቀቅ ለታቀዱ ሌሎች የልማት ሥራዎችን ተነሳሽነትን ይፈጥራል።