የትምህርት ጊዜ ብክነትን ለማስቀረት ወላጆች ልጆቻቸውን በወቅቱ ወደ ትምህርት ቤት መላክ ይገባቸዋል።

2
እንጅባራ: መስከረም 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር እንጅባራ ከተማ የ2018 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ ተጀምሯል።
በባሁንክ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተገኝተው የመማር ማስተማር ሥራውን ያስጀመሩት የእንጅባራ ከተማ አሥተዳደር ትምህርት ጽሕፍት ቤት ኀላፊ ዳኛቸው ጥላሁን በከተማ አሥተዳደሩ በሚገኙ 30 የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች የ2018 የትምህርት ዘመን የመማር ማስተማር ሥራ መጀመሩን ተናግረዋል።
ትምህርት ቤቶችን ለመማር ማስተማር ምቹ ለማድረግ የሚያስችሉ ተግባራት በክረምት ወራት ተከናውነዋልም ነው ያሉት።
የትምህርት ጊዜ ብክነትን ለማስቀረት ወላጆች አስፈላጊ የትምህርት ቁሳቁሶችን አሟልተው ልጆቻቸውን በወቅቱ ወደ ትምህርት ቤት እንዲልኩም ኀላፊው ጠይቀዋል።
የባሁንክ አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራንም የመማር ማስተማር ሥራውን በተሻለ መንፈስ ለመጀመር ዝግጅት አድርገው ወደ ትምህርት ቤት መመለሳቸውን ተናግረዋል።
ተማሪዎችን በዕውቀት እና በሥነ ምግባር የማነጽ ኀላፊነታቸውን በአግባቡ ለመወጣት ቁርጠኛ መኾናቸውንም መምህራኑ ገልጸዋል።
በከተማ አሥተዳደሩ በትምህር ዘመኑ ከ25 ሺህ በላይ ተማሪዎች በትምህርት ገበታ ላይ ይገኛሉ ተብሎም ይጠበቃል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleግድቡ ታሪክ እና ትርክትን የለወጠ ነው።
Next articleየትምህርት ሂደቱ በታቀደው ጊዜ መጀመሩ ተገቢውን የትምህርት ሽፋን ለመስጠት ያስችላል።