የ‎ግድቡ መጠናቀቅ ኢትዮጵያውያን ሲተባበሩ ማንም የማያስቆማቸው እንደኾነ ለዓለም ያሳየ ነው።

1

ባሕር ዳር፡ መስከረም 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕርዳር ከተማ አሥተዳደር የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር የውይይት መድረክ እየተካሄደ ነው።

 

በመድረኩ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ኢትዮጵያ ቀደምት የሰው ዘር መገኛ ባለ ብዙ ታሪክ ሀገር ናት።

 

ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው የኢትዮጵያን ማደግ የማይፈልጉ አካላት በጀመረችው የሥልጣኔ እና የዕድገት መንገድ እንዳትቀጥል ጫና ሲያደርጉ ቆይተዋል ብለዋል።

 

የውስጥ እና የውጭ ጠላቶች ኢትዮጵያ በእርስ በእርስ ጦርነት እንድትታመስ አጀንዳ እየሰጡ የሀገሪቱ ልማት ወደፊት እንዳይራመድ ሢሠሩ መቆየታቸውንም አንስተዋል።

 

አሁን ግን በዓባይ ግድብ የመጠቀም መብቷን አረጋግጣለች፤ አባቶችም ሲቆጩበት የነበረውን ዓባይን ሀገሪቱ በራስ አቅም ለመገደብ መብቃቷን ነው ያብራሩት።

 

ግድቡ በርካታ ችግሮችን አልፎ ከዚህ መድረሱን ያነሱት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው የግድቡ መጠናቀቅ ኢትዮጵያውያን ሲተባበሩ ማንም የማያስቆማቸው ለመኾኑ ለዓለም አሳይተውበታል ነው ያሉት።

 

ከግድቡ ብስራት ጎን ለጎን ኢትዮጵያን ወደ ከፍታ የሚወስዱ በርካታ ታላላቅ ፕሮጀክቶች ይፋ ኾነዋል ብለዋል። የግድቡ መጠናቀቅ ግን ወደፊትም በብርታት ለመሥራት አቅም የሚፈጥር ስለመኾኑ አስገንዝበዋል።

 

በመድረኩም የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅ እና ግድቡ ለኅብረተሰቡ ያለው ምጣኔ ሃብታዊ እና ፖለቲካዊ አንድምታ ምንድን ነው?በሚል የመነሻ ጹሑፍ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ነው።

 

ዘጋቢ፦ ፍሬሕይወት አዘዘው

 

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

 

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ‘አይችሉም’ የሚለውን አስተሳሰብ የሰበረ እና የኢትዮጵያውያንን ሥነ-ልቦና ከፍታ ላይ ያወጣ ነው።
Next articleየ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመኑ ትምህርት መጀመሩን ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።