የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ‘አይችሉም’ የሚለውን አስተሳሰብ የሰበረ እና የኢትዮጵያውያንን ሥነ-ልቦና ከፍታ ላይ ያወጣ ነው።

1

ባሕር ዳር፡ መስከረም 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ጤና ቢሮ በባሕርዳር ከተማ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ምረቃትን አስመልክቶ የእንኳን ደስ አላችሁ መድረክ አዘጋጅቶ ውይይት አድርጓል።

 

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የክልሉ የጤና ቢሮ ላፊዎች፣ የማኔጅመንት አባላት እና ሌሎች ሠራተኞች ተገኝተዋል።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የጤና ቢሮ ኀላፊ አብዱልከሪም መንግሥቱ፣ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ብቻ የተገነባ የአብሮነት እና የአንድነት ምሰሶ መኾኑን ገልጸዋል።

 

ግድቡ የኢትዮጵያን ችግር የሚፈታ፣ በዓለም አደባባይ የኢትዮጵያን ኩራት ያጎናጸፈ እና የሀገሪቱን ሰንደቅ ከፍ ያደረገ ትልቅ ታሪክ ነው ብለዋል።

 

“ይህ ግድብ የሉዓላዊነታችን መገለጫ እና የልማታችን ማንሰራሪያ ነው” ያሉት አቶ አብዱልከሪም ግድቡ የውጭ እና የውስጥ ጠላቶችን ያሳፈረ፣ ‘አይችሉም’ የሚለውን አስተሳሰብ የሰበረ እና የኢትዮጵያውያንን ሥነ-ልቦና ከፍታ ላይ ያወጣ ነው ብለዋል።

 

ግድቡ ከእናቶች እስከ ሕጻናት፣ ከአዛውንት እስከ ወጣት በመላ ኢትዮጵያውያን ተሳትፎ የተገኘ ትልቅ ስኬት እንደኾነም ገልጸዋል።

 

ዘጋቢ: ሰመሃል ፍስሐ

 

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

 

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበምዕራብ ጎንደር ዞን ትምህርት ተጀምሯል።
Next articleየ‎ግድቡ መጠናቀቅ ኢትዮጵያውያን ሲተባበሩ ማንም የማያስቆማቸው እንደኾነ ለዓለም ያሳየ ነው።