
ጎንደር፡ መስከረም 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ አሥተዳደር የ2018 ዓ.ም የመማር ማስተማር ሥራ ተጀምሯል።
የማስጀመሪያ መርሐ ግብሩም በመሠረት አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ነው የተካሄደው።
በመርሐ ግብሩ ነባር ተማሪዎች ለአዲስ ተማሪዎች ችቦ በማብራት የእንኳን ደኅና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ልክ እንደ መሠረት አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሁሉ በከተማዋ የሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች መደበኛ የመማር ማስተማር ሥራ መጀመራቸውን የከተማ አሥተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ስንታየሁ ነጋሽ ለአሚኮ ተናግረዋል።
የመማር ማስተማር ሥራን በወቅቱ ማስጀመር መቻሉ የሚጠበቅን ውጤት ለማሳካት እንደሚያስችልም አቶ ስንታየሁ አንስተዋል።
ትምህርት በወቅቱ መጀመሩ የትምህርት ይዘቶችን በሚገባ ለመሸፈን እንደሚያግዝ በመሠረት አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር ወንደወሰን ልጃለም ተናግረዋል።
የመሠረት አንደኛ እና መካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ አምሳል ዋናቸው ትምህርት በመጀመሩ መደሰታቸውን የተናግራለች።
ትምህርት በወቅቱ መጀመሩ ጊዜያቸውን በአግባቡ ለመጠቀም እና ውጤታማ ለመኾን እንደሚያግዛቸውም ነው የጠቆመችው።
ዘጋቢ፦ ማህደር አድማሴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!