
ደሴ: መስከረም 05/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የመማር ማስተማር ሂደቱ በከተማ አሥተዳደሩ በሚገኙ በ122 የመንግሥት እና የግል ትምህርት ቤቶች በይፋ መጀመሩን ነው የከተማ አሥተዳደሩ ትምህርት መምሪያ ኀላፊ ፍቅር አበበ የተናገሩት።
በከተማ አሥተዳደሩ 62 ሺህ 100 ተማሪዎች ለመማር መመዝገባቸውንም አቶ ፍቅር አስታውሰዋል።
ከአሚኮ ጋር ቆይታ የነበራቸው ወላጆች በመጀመሪያ ቀን ልጆችን ወደ ትምህርት ቤት መውሰድ ልዩ ትዝታ እንዳለው ገልጸዋል።
የከተማችን ሰላም በመረጋገጡ ልጆቻችን ለአፍታም ከትምህርት ገበታ ተነጥለው አያውቁም ያሉት የተማሪ ወላጆች ለትምህርት ስኬት ሁሉም በጋራ እንዲሠራ ጠይቀዋል።
ዘጋቢ፦ ደምስ አረጋ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!