ለሕዝብ ተጠቃሚነት እንደሚሠሩ ጀማሪ እና መካከለኛ መሪዎች ገለጹ።

5

ጎንደር፡ መስከረም 04/2018 ዓ.ም (አሚኮ) “ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ መልዕክት የብልጽግና ፓርቲ ያለፋት ዓመታት እና የቀጣይ የትኩረት መስኮች በማስመልከት ለጀማሪ እና መካከለኛ መሪዎች በጎንደር ከተማ ሲሰጥ የነበረው ሥልጠና ተጠናቅቋል።

የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋ መኮንን ሥልጠናው የተሠሩ ሥራዎችን ለማበረታታት፣ በድክመት የሚታዩትን ለማረም እና አቅም ለማጎልበት ያለመ ነው ብለዋል።

ኀላፊው ጀማሪ እና መካከለኛ መሪዎች በሥልጠናው ያገኙትን ተሞክሮ በመጠቀም ለሕዝብ ተጠቃሚነት እንዲሠሩ ዕድል ይፈጥራል ነው ያሉት።

ለጀማሪ እና መካከለኛ መሪዎች የሚሠጠው ሥልጠና በቀጣይም እስከ ታች የማውረድ ሥራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ኀላፊው ተናግረዋል።

ለመሪዎቹ ሲሰጥ የቆየው ሥልጠና ሁሉም እኩል ግንዛቤ ፈጥሮ ሕዝብን የሚጠቅሙ ሥራዎችን ለመሥራት እንደሚያግዝ በብልጽግና ፓርቲ ቅንጫፍ ጽሕፈት ቤት የዞብል ክፍለ ከተማ የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ደሞዝ ስመኝ ገልጸዋል።

በብልጽግና ፓርቲ ቅንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአራዳ ክፍለ ከተማ የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ጌታቸው እሸቴ መሪዎች ሀገሪቱ ያለችበትን ሁኔታ በመረዳት ለሕዝብ የሚጠቅሙ ተግባራትን ለመከወን ሥልጠናው አጋዥ ነው ብለዋል።

መሪዎቹ ከሥልጠናው ያገኙትን ተሞክሮ በመጠቀም ለሕዝብ ተጠቃሚነት እንደሚሠሩም ነው የገለጹት።

ዘጋቢ:- ዳንኤል ወርቄ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሃብቷን የመጠቀም መብቷን ያረጋገጠችበት ነው።
Next article“ሕዳሴ የአብሮነታችን ዋስትና የቁጭታችን መቋጫ፣ የነገዋ ኢትዮጵያ ተስፋ ብርሃን ነው” አቶ ይርጋ ሲሳይ