ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሃብቷን የመጠቀም መብቷን ያረጋገጠችበት ነው።

5
እንጅባራ: መስከረም 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ከተለያዩ ወረዳዎች እና ከተማ አሥተዳደሮች የተውጣጡ የኅብረተሰብ ተወካዮች የግድቡን መመረቅ በእንጅባራ ከተማ በውይይት አክብረዋል።
የመላው ኢትዮጵያውያን የላብ እና የደም አሻራ የታታመበት እና የይቻላል ምልክት የኾነው ታላቁ ኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ተጠናቅቆ መመረቅ በመላው ኢትዮጵያውያን ዘንድ ልዩ ደስታን ፈጥሯል።
የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ ቴዎድሮስ እንዳለው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከኃይል ማመንጫነቱ ባሻገር “ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሃብቷን የመጠቀም መብቷን ያረጋገጠችበት” ታሪካዊ ፕሮጀክት መኾኑን ተናግረዋል።
ግድቡ መላው ኢትዮጵያውያንን በአንድነት ያሰባሰበ፣ የመንግሥት የዲፕሎማሲ ብልጫ የታየበት፣ የብልጽግና ማስፈንጠሪያ ዳግማዊ ዓድዋ ነው ብለዋል።
በሕዳሴ ግድብ ግንባታ ወቅት የታየው የኢትዮጵያውያን አንድነት እና መነሳሳት በሌሎችም ልማቶች ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበትም አስገንዝበዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎችም ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለፍጻሜ በመብቃቱ መደሰታቸውን ተናግረዋል።
ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን በዓባይ ወንዝ ላይ ለነበራቸው የዘመናት ቁጭት የተከፈለ ካሳ መኾኑንም አንስተዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የላብ እና የደም ውጤት ነው ያሉት አስተያየት ሰጭዎቹ ገንዘባችንን፣ ጉልበታችንን እና ዕውቀታችንን አስተባብረን በሌሎችም ልማቶች በጋራ እንቆማለን ነው ያሉት።
ዘጋቢ:- ሳሙኤል አማረ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የጥቁር ሕዝቦች ኩራት እና ምልክት ነው።