
ገንዳ ውኃ፡ መስከረም 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎንደር ዞን የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መመረቅን አስመልክቶ ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ጋር የንቅናቄ መድረክ በገንዳ ውኃ ከተማ ተካሂዷል።
የዘመናት ልፋታቸው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተጠናቅቆ ለምርቃት በመብቃቱ ደስተኛ መኾናቸውን የንቅናቄ መድረኩ ተሳታፊዎች ተናግረዋል።
ማኅበረሰቡ ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ እንዲነግድ እና እንዲሠራ ሰላም ወሳኝ በመኾኑ ለሰላም መሥራት እንደሚገባም ገልጸዋል።
ሰላምን ለማጽናት እንደሠለጠነ ሰው ችግሮችን በውይይት መፍታት እንደሚያስፈልግም ተሳታፊዎች ተናግረዋል። ለሰላም መከበርም ከመንግሥት ጎን እንደሚቆሙም አረጋግጠዋል።
ሰላምን በማስከበር በቀጣይ በሚሠሩ ሀገራዊ ፕሮጀከቶች ላይ የበኩላቸውን ድርሻ እንደሚወጡም ገልጸዋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የጥቁር ሕዝቦች ኩራት እና ምልክት መኾኑንም ተናግረዋል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ተወካይ እና የዞኑ ሰላም እና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ደረሰ አዱኛ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አብሮነትን የሚያጠናክር፣ አንድነትን የሚያሰፋ፣ ልዩነትን የሚያጥብ እና ሰላምን የሚያጸና የማንሠራራት ጅማሮ መኾኑን ገልጸዋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከታችኛው ታፋሰስ ሀገራት ጋር በኢኮኖሚው፣ በፖለቲካው፣ በዲፕሎማሲው ዘርፍ የሚያስተሳስር እና ኢትዮጵያን ከፍ የማድረግ አቅም እንዳለውም አስገንዝበዋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከኤሌክትሪክ ኀይል ማመንጨት ባለፈ የኢኮኖሚዊ ጠቀሜታ እንዳለውም ገልጸዋል።
የውል ትሪክትን፣ ማኅበራዊ አንድነት እና ትስስርን የሚጠናክር መኾኑንም አንስተዋል።
ማኅበረሰቡ ከእርስ በእርስ ግጭት በመውጣት በውይይት ችግሮችን መፍታት፤ ሰላምን በማጠናከር ልማት ላይ ማተኮር እንደሚገባውም አሳስበዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!