ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የዘመናት ቁጭት ስኬት ነው።

4
ደብረማርቆስ፡ መስከረም 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የታላቁ የኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን አስመልክቶ ”ዕምርታ እና ማንሠራራት” በሚል መሪ መልዕክት ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ውይይት አካሂዷል።
በውይይቱ ታላቁ የኢትዮጵ ሕዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን ላባቸውን እና ደማቸውን የገበሩበት ውጤት መኾኑ ተብራርቷል። በተባበረ ክንድ በአንድ ድምጽ የቆመ ፕሮጀክት እንደኾነም ነው የተገለጸው።
ግድቡ የወል ትርክት ግንባታ ላይ ትልቅ ትርጉም የሰጠ እና ሀገራዊ ገጽታን የገነባ መኾኑም ተብራርቷል።
የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ አበባው ግዛቸው ተግዳሮቶች በበዙባቸው ባለፉት ሰባት ዓመታት የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ጨምሮ በሁለንተናዊ መሥክ ድል ተመዝግቧል ብለዋል። በኅብረት መቻል የተረጋገጠበት መኾኑን አስገንዝበዋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከሌሎች ልማቶች ሁሉ ለየት የሚያደርገው በራስ አቅም የተሠራ፤ የሀገር እና ሕዝብን ጥንካሬ ያሳየ ዳግም ዓደዋ እና የማንሠራራት ምልክት ነው ብለዋል።
የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የአደረጃጀት ዘርፍ ኀላፊ ላቀች ሰማ የግድቡ መጠናቀቅ የአንድነት ማሳያ እና የትብብር ውጤት መኾኑን አስገንዝበዋል።
ዘላቂ ሰላም ላይ በመሥራት የቀጣይ ፕሮጀክቶችን እውን ማድረግ ይገባልም ብለዋል።
በውይይቱ የተሳተፉ እናቶች ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ “የዘመናት ቁጭታችን ስኬት የመቀነታችንም ፍሬ ነው” ብለዋል፡፡
የሃይማኖት አባቶቹ በበኩላቸው ለሕዳሴ ግድብ ለደከሙ፣ ዋጋ ለከፈሉ መሪዎች እና ሙያተኞችም ክብር ይገባል ነው ያሉት።
የልማትን ትሩፋት እና ፍሬ ለመጠቀም ሰላም ወሳኝ በመኾኑ ሰላም እንዲረጋጥ እንደሚፈልጉ እና ለዚህም የድርሻቸውን እንደሚወጡም አብራርተዋል።
በውይይቱ የጸጥታ አካላት እና ሌሎች የኅብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleተማሪዎችን ማገዝ ሀገርን ማገዝ ነው።
Next articleየታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የጥቁር ሕዝቦች ኩራት እና ምልክት ነው።