
ፍኖተ ሰላም፡ መስከረም 03/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ”ኢትዮጵያን ወደ ተምሳሌት ሀገር” በሚል መሪ መልዕክት ለመሪዎች ሥልጠና እየሰጠ ነው።
የምዕራብ ጎጃም ዞን ብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ሙላት ጌታቸው ብልጽግና ፓርቲ ሕዝቡን በማነቃቃት የማይደፈሩ የልማት ሥራዎችን ማከናወኑን ተናግረዋል።
ባለፉት ጊዜያት ያሉ ፀጋዎችን በመለየት ጥቅም ላይ ለማዋል በርካታ ሥራዎች ተሠርተዋል ነው ያሉት።
ሥልጠናው የሕዝብን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ መነሳሳትን እንደሚፈጥርም ተናግረዋል።
የምዕራብ ጎጃም ዞን መሬት መምሪያ ኀላፊ እና የፍኖተ ሰላም ቀጣና የሥልጠና አስተባባሪ ጥበቡ አማረ መሪዎች ወቅታዊ ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን በመረዳት የሀገሪቱን ዕድገት ወደተሻለ ደረጃ ማሸጋገር እንደሚገባቸውም ገልጸዋል።
ሥልጠናው የመሪዎችን አቅም በማሻሻል የታቀዱ የልማት፣ የሰላም እና የመልካም አሥተዳደር ሥራዎችን ለማሳካት ያግዛልም ብለዋል።
ዛሬ የተጀመረው ሥልጠና ለተከታታይ ሦሥት ቀናት እንደሚቆይም ነው የተገለጸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!