ትላልቅ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶችን ለማሳካት መጭውን ጊዜ አስቦ መሥራት ይገባል።

1
ደብረ ማርቆስ: መስከረም 02/2018 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ያለፉት ዓመታት ጉዞ እና የቀጣይ ዓመታት የትኩረት መስኮች ላይ ግንዛቤ የሚፈጥር ሥልጠና ጀምሯል።
ሥልጠናው የጋራ አቋም በመያዝ የሀገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም እና ክብር ለማስጠበቅ ለመሪዎች ግንዛቤ የሚፈጠርበት መኾኑን በብልጽግና ፓርቲ የደብረ ማርቆስ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ አበባው ግዛቸው ገልጸዋል።
”ኢትዮጵያ ወደ ተምሳሌት ሀገር ” በሚል መሪ መልዕክት የሚሰጠው ሥልጠና በከተማው የሚገኙ የመምሪያ፣ የክፍለ ከተማ እና የቀበሌ አመራሮች እየተሳተፉበት ነው። ሥልጠናው ባለፉት ዓመታት የተገኙ ውጤቶችን ለማስረፅ እና የቀጣይ ሀገራዊ አጀንዳዎችን በውል ተገንዝቦ መግባባት የሚደረስበት እንደኾነም ተናግረዋል። ከዚህ በፊት በፓርቲው ቃል የተገቡ ሀገራዊ ጥቅሞችን ለማስጠበቅ የተቀረፁ የትኩረት ነጥቦችን ለይቶ ለመፈፀም ያለመ ስለመኾኑም አስገንዝበዋል።
በሥልጠና መድረኩ ላይ የተገኙት የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ተወካይ ይኸነው አበባው ባለፉት አምስት ዓመታት በችግር ውስጥ ኾኖ የተሠሩ ሥራዎች ላይ ሰፊ ግንዛቤ በመፍጠር በቀጣይ የታቀዱ ትላልቅ ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶች ለማሳካት በቁርጠኝነት መሥራት ከመሪዎች ይጠበቃል ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleሥር ነቀል ጥገና የተደረገለት የደሴ ሙዚየም
Next articleተግዳሮቶችን በመሻገር የሀገር ዕድገትን የሚያፋጥኑ ሥራዎችን መሥራት ይገባል።