በአገው ግምጃ ቤት ከተማ አሥተዳደር የተለያዩ መሠረተ ልማቶች ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ኾኑ።

6
እንጅባራ: ጳጉሜን 05/2017 ዓ.ም (አሚኮ) መሠረተ ልማቶቹ በመንግሥት መደበኛ በጀት እና በኅብረተሰብ ተሳትፎ የተገነቡ ናቸው። ለመሠረተ ልማቶቹ ከ26 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸዋል ተብሏል።
የከተማው ነዋሪዎችም የተገነቡ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች የኅብረተሰቡን የኑሮ ጫና የሚያቃልሉ መኾናቸውን ተናግረዋል።
መሠረተ ልማቶቹ ተገቢውን አገልግሎት እንዲሰጡ ጥበቃ እና እንክብካቤ እንደሚያደርጉላቸውም ገልጸዋል።
የአገው ግምጃ ቤት ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ወርቃየሁ አስረስ ተመርቀው ለአገልግሎት ከበቁ መሠረተ ልማቶች መካከል ከ260 ሜትር በላይ የኮብል መንገድ፣ ዲጂታል የመረጃ አያያዝ ቋት፣ መለስተኛ ድልድዮች፣ የወጣቶች የሥራ እድል መፍጠሪያ ሸዶች እና የመብራት መሠረተ ልማት ዝርጋታ እንደሚገኙበት ገልጸዋል።
የተገነቡ መሠረተ ልማቶች ቀበሌን ከቀበሌ የሚያስተሳስሩ እና የከተማዋን የወደፊት የማደግ ተስፋ የሚያፋጥኑ እንደኾነም አንስተዋል።
የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ዋና አሥተዳዳሪ ቴዎድሮስ እንዳለው ዛሬ ግንባታቸው ተጠናቀው ለአገልግሎት የበቁ መሠረተ ልማቶች የኅብረተሰቡ የአንድነት እና የሰላም ውጤቶች መኾናቸውን ተናግረዋል።
አንድ ስንኾን ያቀድነውን ማሳካት እንችላለን ያሉት ዋና አሥተዳዳሪው ለዚህ ደግሞ ታላቁ የኢትዮጵያ ኅዳሴ ግድብ ማሳያ ነው ብለዋል።
በከተማዋ አሁንም በርካታ የመሠረተ ልማት ፍላጎቶች መኖራቸውን ያነሱት ዋና አሥተዳዳሪው የመንግሥት እና የኅብረተሰቡን አቅም አቀናጅቶ በመጠቀም የልማት ጥያቄዎችን ለመመለስ በትኩረት ይሠራል ነው ያሉት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous article“ታላቁን የሕዳሴ ግድባችንን ስናይ ለልማት እንበረታለን” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
Next article“2018 የኢትዮጵያን ማንሠራራት የበለጠ ሥር እና መሠረት የምናስይዝበት ዓመት ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)