
ፍኖተ ሰላም: ጳጉሜን 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የምዕራብ ጎጃም ዞን አሥተዳደር ጳጉሜ 4 የማንሠራራት ቀንን ”ዘላቂ ልማት ለሀገራዊ ማንሠራራት” በሚል መሪ መልዕክት የዞኑ አመራሮች እና መንግሥት ሠራተኞች፣ የመከላከያ ሠራዊት አመራሮች እና አባላት በተገኙበት በፓናል ውይይት ተከብሯል።
በመድረኩ የተገኙት በብልፅግና ፓርቲ የምዕራብ ጎጃም ዞን ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት የፖለቲካ እና አቅም ግንባታ ዘርፍ ኀላፊ ሙላት ጌታቸው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ጠላቶች አንገት ያስደፋ እና ድህነትን የምንፀየፍበት ፕሮጀክት ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያ በሁሉም ዘርፍ ማንሠራራቷን በግልፅ ያሳየችበት እና ያረጋገጠችበት ልዩ ዕለት መኾኑንም ጠቁመዋል።
የፓናል ውይይቱ ተሳታፊዎች እንዳሉት በርካታ ፈተናዎችን በመታገል ሕዳሴ ግድቡን እውን ማድረግ ተችሏል።
የውጭ ጠላቶቻችን ለበርካታ ዓመታት አጀንዳዎቻቸውን ለማስፈፀም ሲታትሩ እጃቸውን የተቆረጡበት የብስራት ቀን መኾኑን አንስተዋል። ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ከራሳችን ለራሳችን በማድረግ ያሳካነው ፕሮጀክት ነው ብለዋል።
የግል ጉዳዮችን ወደ ጎን በመተው በሀገራዊ ጉዳዮች ተባብረን በመሥራት የትኛውንም ልማት ማሳካት እንችላለን ነው ያሉት።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን