የአማራ ክልል ምክር ቤት እና በአማራ ክልል የሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በጋራ ለመሥራት የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።

6

ባሕር ዳር: ጳጉሜን 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ስምምነቱ በአቅም ግንባታ፣ በትምህርት፣ በጥናት ምርምር፣ በፕሮጀክት ቀረጻ እና ሌሎችንም ሥራዎች ዙሪያ በመደጋገፍ ለመሥራት መኾኑ ተገልጿል።

 

ስምምነቱን የአማራ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ አማረ ሰጤ እና የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና የአማራ ክልል ዩኒቨርሲቲዎች ፎረም ሰብሳቢ ተወካይ መንገሻ አየነ (ዶ.ር) ናቸው የፈረሙት።

 

ዘጋቢ፦ ዋሴ ባዬ

 

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

👇👇👇

https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation

 

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous article“ጎንደር ከጉስቁልና ወጥታ እያንሠራራች ነው” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ቻላቸው ዳኘው 
Next articleተባብረን በመሥራት የትኛውንም ልማት ማሳካት እንችላለን።