
ደሴ: ጳጉሜን 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዋጋ የከፈለበት የአንድነት ተምሳሌት መኾኑን ነዋሪዎቹ ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ያስተሳሰረ እና የሀገር ብልጽግና የሚረጋገጥበት ቁልፍ ፕሮጀክት መኾኑን አስተያየት ሰጭዎቹ ገልጸዋል።
ትብብር ካለ የማይሳካ ነገር አለመኖሩን ማሳያና እና ‘የእንችላለን መንፈስ’ እውን የኾነበት ነውም ብለዋል።
አስተያዬታቸውን ለአሚኮ ከሰጡ የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪዎች መካከል ወይዘሮ ገነት አበራ ”የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ለኛ ለኢትዮጵያውያን የህልውናችን መሠረት የአንድነታችን ማሳያ ነው” ብለዋል።
ሌላኛው አስተያየት ሰጭ ወጣት ኤፍሬም ገብረ ብርሃን ”ግድቡ ከጅማሮው እስከ ፍፃሜው እንዳይገደብ ከውጭም ከውስጥም ብዙ ሴራዎች ሲሸረቡበት የነበረ ቢኾንም በኢትዮጵያውያን የተባበረ ክንድ እውን ኾኗል ነው ያለው።
ተጠናቅቆ ለመመረቅ በመብቃቱም የተለየ ደስታ እንደፈጠረበት ተናግሯል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ተጠናቅቆ በመመረቁ በሀገሩ ኩራት እንዲሰማው እንዳደረገውም አብራርቷል።
ነዋሪዎቹ ለአሚኮ በሰጡት ሃሳብ እንዳሉት ሌሎች ሀገርን ከፍ ለሚያደርጉ ግዙፍ ፕሮጀክቶች በጋራ መቆም ይገባል።
ዘጋበ:- ደምስ አረጋ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇
https://linktr.ee/AmharaMediaCorporation
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!