ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በጋራ መሥራትን ያሳየ የዘመኑ ትሩፋት ነው፡፡

3
ጎንደር: ጳጉሜን 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አሚኮ ያነጋገራቸው የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች የመቻል ማሳያ የኾነው የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመመረቁ ደስታቸውን ገልጸዋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ እንዲጠናቀቅ በሚችሉት ሁሉ ከሕጻን እስከ አዛውንት ድጋፍ ሲያደርጉ መቆየታቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል።
ትላልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶችን በራስ አቅም ጀምሮ መጨረስ እንደሚቻል የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ማሳያ መኾኑን የጠቀሱት ነዋሪዎቹ በቀጣይም ሌሎች ፕሮጀክቶችን ለመገንባት ልምድ የተቀሰመበት መኾኑን አስረድተዋል።
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዳግማዊ ዓድዋ ነው ያሉት ነዋሪዎቹ ሀገራዊ አንድነትንም ለማምጣት እንደሚያስችል ገልጸዋል።
አስተያየት ሰጭዎቹ ለመላው ኢትዮጵያውያን እና ለኢትዮጵያ ወዳጆች ሁሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ : ዳንኤል ወርቄ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleግድቡ የእናቶች መቀነት አሻራ ውጤትም ነው።
Next articleየማንሰራራት ቀንን በታላቁ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ ምረቃ ዕለት ማክበር የተለየ ስሜትን እና ተስፋን ይፈጥራል፡፡