
ደብረብርሃን: ጳጉሜን 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ጳጉሜን 4/2017 ዓ.ም በአካል ብቃት እንቅስቃሴው ላይ የተገኙት የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት በባለፉት ዓመታት በከተማው የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ከአካባቢ አልፈው ለሀገር ተኪ ምርት በማምረት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከቱ እንደሚገኙ ተናግረዋል።
በከተማው የተጀመረውን ሁለንተናዊ ዕድገት አጠናክሮ መቀጠል ጊዜው የሚጠይቀው ተግባር መኾኑንም አንስተዋል።
የሕዳሴው ግድብ ፕሮጀክት መጠናቀቁ የኢትዮጰያ የማንሰራራት ዘመን እና የለውጥ ሽግግር ማሳያ መኾኑንም ገልጸዋል።
የሕዳሴው ግድብ በመጠናቀቁ ለመላው ኢትዮጵያውያን የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል።
በሀገር ደረጃ የታቀደውን የአሻጋሪ እና የዘላቂ ልማት ዕቅድ ዕውን እንዲኾን ኅብረተሰቡ እና ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን አስተዋጽዖ እንዲያደርጉም ጠይቀዋል።
ዘጋቢ፦ ዮናስ ታደሰ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!