
ባሕር ዳር: ጳጉሜን 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) አድዋ እና ዓባይ ኢትዮጵያዊያን አብረው፣ ድር እና ማግ ኾነው የሠሯቸው ህያው ሐውልቶች ናቸው።
ዓባይ እና ዓድዋ በርካታ የሚያመሳስሏቸው ጉዳዮችም ያሏቸው የማይፋቁ አሻራዎች ሊባሉ ይችላሉ።
አድዋ የቅኝ ግዛት ቅዠትን ያመከንበት ሲኾን ዓባይ ደግሞ የቅኝ ግዛት ውልን የቀደድንበት ነው ማለት ይቻላል።
ይህ ብቻም አይደለም አድዋ የወቅቱ ኃያላን ሀገራት መሣሪያ የከለከሉን ግን ደግሞ በጋሻ እና በጦር ድል የነሳንበት ሲኾን ዓባይ ደግሞ ያደጉ ሀገራት ገንዘባቸውን ያሸሹብን ግን ካለችን አዋጠን የገነባነው መኾኑም ያመሳስላቸዋል።
አድዋ በጦር ፊት ተሰልፈን መስዋዕት የከፈልንበት ነው፤ ዓባይ ደግሞ በልማት ቆርጠን ሕይወት የገበርንበት ትልቁ ፕሮጀክታችን ነው። ዓድዋ ኃያላን ነን የሚሉ የዶለቱብን ግን በጀግንነት የተወጣነው፤ ዓባይ ደግሞ ታሪካዊ ጠላቶች እንዳንሠራው የኳተኑበት ግን በዲፕሎማሲ የረታንበት ህያው አሻራችን ነው ማለት ይቻላል።
በጥቅሉ አድዋ እና ዓባይ የኢትዮጵያ ልኮች የሀገሪቱ ምጣኔዎች ናቸው ቢባሉ ሀቅ ይኾናል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!