ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የምረቃ ሥነ-ሥርዓት በጉባ እየተካሄደ ነው፡፡

6
ባሕር ዳር: ጳጉሜን 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቅቆ የምረቃ ሥነ ሥርዓቱ በጉባ እየተካሄደ ነው፡፡ በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች፣ የዓለም አቀፍ እና አህጉር አቀፍ ድርጅት ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡
በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ከታደሙት የሀገር መሪዎች፣ የአህጉር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ ድርጅቶች ተወካዮች መካከልም፡-
👉 የጅቡቲ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት እስማኤል ዑመር ጊሌ
👉 የደቡብ ሱዳን ፕሬዝዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት
👉 የሶማሊያ ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼክ መሐመድ (ዶ.ር)
👉 የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ (ዶ.ር)
👉 የባርባዶስ ሪፐብሊክ ጠቅላይ ሚኒስትር ሚያ አሞር ሞትሊ
👉 የኢስዋቲኒ ግዛት ጠቅላይ ሚኒስትር ራስል ሚሚሶ ድላሚኒ
👉 የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ኮሚሽነር አሊ የሱፍ
👉 የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሐፊ እና የተባበሩት መንግሥታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ዋና ፀሐፊ ክላቨር ጌቴቴ
የምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ከዋዜማው ምሽት ጀምሮ በልዩ ልዩ መርሐ ግብሮች እየተካሄደ ነው፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous article“ይህ ቀን ለኢትዮጵያ የትንሣኤ ቀን ነው” ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)
Next articleየብሔራዊ ቃል ኪዳን የኾነው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ