
ሁመራ: ጳጉሜን 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በዚህ የደስታ መግለጫ ሥነ ሥርዓት የሁመራ ከተማ አሽከርካሪዎች የተሽከርካሪ ሰልፍ አድርገዋል።
በሰልፉ ላይ ከተገኙት መካከል የባጃጅ አሽከርካሪው ዮሐንስ አዛናው ግድቡ የሕዝብ አንድነት ፍሬ መኾኑን ገልጿል።
የሁመራ ከተማ ነዋሪው አቶ ነጋ ባንቲሁን በግድቡ መመረቅ መደሰታቸውን ገልጸው ግድቡን ማየት ምኞታቸው መኾኑን ጠቁመዋል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የዞኑ ሀገረ ስብከት ዋና ሥራ አሥኪያጅ መጋቢ ሐዲስ መምህር ዜናዊ አሸተ እና የዞኑ ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ምክትል ኀላፊ ጌታቸው ሙሉጌታ በደስታ መግለጫ ሥነ ሥርዓቱ ላይ ተገኝተው ደስታቸውን ገልጸዋል።
አስተያየት ሰጭዎቹ ግድቡ ኢትዮጵያን ታላቅ ሀገር እንደሚያደርጋት እና የኢትዮጵያን ሕዝብ አንድ እንደሚያደርግም ለአሚኮ ተናግረዋል።
ነዋሪዎች የግድቡን ግንባታ መጠናቀቅ በጋራ ጥረት እና አንድነት የተገኘ ታላቅ ስኬት አድርገው እንደሚመለከቱትም ነው ያብራሩት።
ዘጋቢ፦ አምሳሉ አሞኘ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!