
ባሕር ዳር: ጳጉሜን 04/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ጳጉሜን 4/2017 ዓ.ም “የማንሠራራት” ቀንን ምክንያት በማድረግ የልማት ሥራዎችን እየጎበኙ ነው።
በጉብኝቱ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አሥተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የማኅበራዊ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የትምህርት ቢሮ ኀላፊ ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
መሪዎቹ የባሕርዳር አውሮፕላን ማረፊያ አዲስ የማስፋፊያ ግንባታን ጎብኝተዋል።
አዲሱ የማስፋፊያ ግንባታ 11ሺህ 171 ሜትር ስኪዮር ስፋት ተርሚናል ያለው ነው።
አዲሱ የማስፋፊያ ግንባታ 150 በ 210 ሜትር ስፋት ያለው የአውሮፕላን ማረፊያም እንዳለው ተገልጿል።
10 መንገዶችን ጨምሮ ፓርኪንግ እና ሌሎች የመሠረተ ልማቶች ያሉት ፕሮጄክትም ነው።
በ24 ሚሊዮን ዶላር እየተሠራ እንደኾነ የተገለጸው ፕሮጄክቱ ግንባታው 64 ነጥብ 18 በመቶ ደርሷል ነው የተባለው።
የቀድሞው የአውፕላን ማረፊያ ማስፋፊያ ተጨምሮበት ነው እየተሠራ የሚገኘው።
ዘጋቢ፦ ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!