“እመርታ ለዘላቂ ከፍታ” በሚል መሪ መልዕክት በኮምቦልቻ ከተማ ጳጉሜን 3 በፓናል ውይይት እና ጉብኝት እየተከበረ ነው። 

3

ደሴ: ጳጉሜን 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በፓናል ውይይቱ ላለፉት ሦስት ዓመታት ማለትም ከ2015 እስከ 2017 ዓ.ም የሥራ አፈጻጸም እንደ ከተማ ተገምግሟል።

የፓናል ውይይቱን የመነሻ ጽሑፍ ያቀረቡት የኮምቦልቻ ከተማ የከተማና መሰረተ ልማት መምሪያ የእቅድና በጀት ቡድን መሪ ሰይድ ይመር እንደገለጹት ከ2015 እስከ 2017 ኮምቦልቻ ከተማ በግብርና፣ በመሰረተ ልማት፣ በኢንቨስትመንት እና ሰላም እምርታዊ ለውጥ አምጥታለች ብለዋል።

ከተማዋ ለጅቡቲ ወደብ እና ለአዲስ አበባ ቅርብ በመኾኗ እንዲሁም የተጀመረው የባቡር መስመር ከተማዋን ለንግድ እና ለኢንቨስትመንት ቀዳሚ ተመራጭ ያደርጋታል ነው ያሉት።

የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ሰላምና ጸጥታ መምሪያ ኀላፊ ኮማንደር ሰይድ አሊ ኮምቦልቻ ከተማ የኢንዱስትሪ ከተማ በመኾኗ ሰላሟ አስተማማኝ እንዲኾን በማድረግ በኢንቨስትመን እና በንግድ እንቅስቃሴዎች ከፍተኛ ለውጥ ተመዝግቧል ነው ያሉት።

ፕሮጀክቶችን ጀምሮ በሙሉ አቅም በመሥራት በፍጥነት እና በጥራት በማጠናቀቅ አዲስ የሥራ ባሕል ተፈጥሯል ያሉት ኮማንደር ሰይድ በቀጣይም ሰላምን የማጽናትና ፕሮጀክቶችን የመፈፀም አቅምን በማሳደግ

በትኩረት ይሠራል ብለዋል።

ዘጋቢ፦ መሐመድ በቀለ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleፈጠራ እና ቴክኖሎጅ ልዩ ትኩረት ተሰጥቶታል። 
Next articleከበዓል ጋር ተያይዞ ሊፈጠሩ ከሚችሉ ወንጀሎች እና አደጋዎች ራስን መጠበቅ ይገባል።