የጳጉሜን 3 የእመርታ ቀን በደሴ ከተማ በተለያዩ ኹነቶች ተከብሯል።

4
ደሴ: ጳጉሜን 03/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በከተማዋ የሌማት ትሩፋት ሥራዎች ውጤታማ መኾናቸውን የሚያሳዩ የግብርና ምርቶች ተጎብኝተዋል።
በከተማ ግብርና የተሠማሩ ነዋሪዎችም ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ሉዓላዊነታቸውን ለማረጋገጥ እየሠሩ መኾናቸውን ተናግረዋል።
ከእለት ፍጆታ አልፈው ከተማ አሥተዳደሩ በሚወስዳቸው የገበያ ማረጋጋት ሥራዎች ምርቶቻቸውን እያቀረቡ እንደኾነም ገልጸዋል።
በዕለቱ የከተማዋ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ የተጎበኘ ሲኾን በተለያዩ ኢንዱስትሪዎች የተመረቱ ምርቶችም ለእይታ ቀርበዋል። እነዚህ ኢንዱስትሪዎች ለሥራ ዕድል ፈጠራ እና የዕውቀት ሽግግር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸው ተመላክቷል።
የደሴ ከተማ አሥተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኀላፊ አለባቸው ሰይድ በከተማዋ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴው እምርታዊ ለውጥ ተመዝግቧል ነው ያሉት።
ባለፈው ዓመት ከ45 ሄክታር በላይ መሬት ለኢንዱስትሪ እና ለአገልግሎት ዘርፎች መተላለፉን የገለጹት ኀላፊው በዚህ ዓመትም ለአምራች እና አገልግሎት ዘርፉ የሚተላለፍ ከ150 ሄክታር በላይ መሬት ለማዘጋጀትን በቅንጅት እየተሠራ መኾኑን ተናግረዋል።
በከተማ አሥተዳደሩ በልማት ለመሳተፍ ፍላጎት ላላቸው ባለሃብቶች ምቹ ኹኔታዎች መኖራቸውን አቶ አለባቸው አስረድተዋል።
የደሴ ከተማ አሥተዳደር ዋና አፈ ጉባኤ አህመድ ሙህዬ ዕለቱን ስናከብር ሰላማችንን በማስቀጠል ማኅበረሰቡ በሁሉም መስክ ተጠቃሚ እንዲኾን ቃል የምንገነባበት ነው ብለዋል።
ዘጋቢ ፦ አንተነህ ፀጋዬ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous article“የጀመርናቸውን በመጨረስ፣ ያለምናቸውንም በመጀመር የኢትዮጵያን እመርታ ለማብሰር እየሠራን ነው” ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው
Next article“የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥ የሉዓላዊነት ጉዳይ ነው” ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)