በኩታ ገጠም የለማ የሰንዴ ሰብል ልማት ተጎበኘ።

2
ደብረ ብርሃን: ጳጉሜን 3/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “እመርታ ለዘላቂ ከፍታ” በሚል መሪ መልዕክት በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ሳሪያ ቀበሌ በኩታ ገጠም የለማ የስንዴ ሰብል ተጎብኝቷል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ ኀላፊ መርሻ አይሳነው በከተማ አሥተዳደሩ በ2017/18 የምርት ዘመን 7 ሺህ 400 ሄክታር መሬት በስንዴ ሰብል መሸፈኑን ተናግረዋል።
በከተማ አሥተዳደሩ ከለማው የስንዴ ሰብል መካከል ከ4 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በኩታ ገጠም መልማቱንም ጠቁመዋል።
በኩታ ገጠም የስንዴ እያለሙ የሚገኙ አርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት ለማጎልበት ሙያዊ ድጋፍ እየተደረገ እንደሚገኝም አንስተዋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ወርቃለማሁ ኮስትሬ አርሶ አደሮችን ከተረጅነት ለማላቀቅ በሚሠራው ሥራ የሰንዴ ልማት ዕምርታዊ ውጤት እያስመዘገበ እንደኾነ ጠቁመዋል።
አርሶ አደሮች በምርት ዘመኑ የተሻለ ምርት እንዲያሰመዘግቡ የሚያስችል ሥራ ይሠራልም ነው ያሉት።
ዘጋቢ፦ ወንድይፍራ ዘውዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን

Previous articleየእንስሳት ተዋፅዖ ምርቶችን በስፋት ለማቅረብ እየተሠራ ነው።‎
Next article“የአብሮነት መገለጫ የኾነው የሩፋኤል በዓል በዓባይ ወንዝ”