በዞኑ ውጤት ማምጣት የቻሉ ሥራዎች ተሠርተዋል።

6
ጎንደር: ጳጉሜን 3/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት “እመርታ ለዘላቂ ልማት” በሚል መሪ መልዕክት የፓናል ውይይት አካሂደዋል።
‎በፓናል ውይይቱ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ፣ ገንዘብ መምሪያ፣ የኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ፣ የማዕድን ሃብት ልማት መምሪያ፣ የገቢዎች መምሪያ እንዲሁም የፕላን እና ልማት መምሪያ ሠራተኞች ተሳትፈዋል።
በመድረኩ የተሳተፉት የማዕከላዊ ጎንደር ዞን የማዕድን ሃብት ልማት የጂኦሎጂ ባለሙያ ሳለአምላክ አምሀ ‎የማዕድን ዘርፉ በዞኑ ለበርካታ ወጣቶች የሥራ ዕድል መፍጠሩን አንስተዋል።
ባለሙያው ሕገወጥ የማዕድን ዝውውርን በመከላከል የማዕድን ሃብትን ለሚፈለገው ዓላማ እንዲውል እየተደረገ መኾኑንም አስረድተዋል።
‎በ2017 ዓ.ም በዞኑ ከ61 በላይ ባለሃብቶች በተለያዩ የሥራ ዘርፎች ለመሰማራት የኢንቨስትመንት ፈቃድ መውሰዳቸውን ነው የጠቆሙት።
የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት መምሪያ ተወካይ ኀላፊ ሸዋንግዛው አበበ ከ30 በላይ ባለሃብቶች ወደ ሥራ መግባታቸውን አመላክተዋል።
የጸጥታ ችግሩ ባለሃብቶች ሙሉ ለሙሉ ወደ ሥራ እንዳይገቡ እንዳደረጋቸውም ጠቁመዋል።
‎ከተለያዩ ተቋማት ጋር ውይይት ማድረጋቸውም የየሴክተሩን አፈፃፀም ከመገምገም ባለፈ ለቀጣይ ሥራ ልምድ የሚቀሰምበት ነው ያሉት ደግሞ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን አሥተዳደር ጽሕፈት ቤት የፕላን እና ልማት ‎መምሪያ ተወካይ ኀላፊ ስማቸው ማዘንጊያ ናቸው።
‎በግብርናው ዘርፍ የተከናወኑ ዘርፈ ብዙ ተግባራት በምግብ ራስን ለመቻል የሚደረገውን ጥረት ሊያሳኩ የሚችሉ እና ውጤት የተመዘገበባቸው መኾናቸውንም አቶ ስማቸው አመላክተዋል።
‎ከውይይቱ ባሻገር በእመርታ ቀን የተሠሩ ሥራዎችን መጎብኘታቸው መነሳሳት እና ለቀጣይ ትግበራ ጉልበት እንደሚኾናቸውም ጠቁመዋል።
‎የመርሐ ግብሩ ተሳታፊዎች በፋሲል አብያተ መንግሥታት ተገኝተው የእድሳት ሂደቱ ምን እንደሚመስል ተመልክተዋል።
‎ዘጋቢ፦ ተስፋዬ ጋሹ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous article“የምሥጢር ቦታ፣ የጥበብ ገበታ”
Next articleጎጅ ልማዳዊ ድርጊቶችን በመከላከል ረገድ ውጤታማ ሥራዎች ተከናውነዋል።