የእመርታ ቀን በባሕር ዳር ከተማ በተለያዩ ኹነቶች እየተከበረ ነው።

3
ባሕር ዳር: ጳጉሜን 3/2017 ዓ.ም (አሚኮ) “እመርታ ለዘላቂ ከፍታ” በሚል የሚከበረው ጳጉሜን 3/2017 ዓ.ም በባሕር ዳር ከተማ በተለያዩ ሁነቶች እየተከበረ ነው።
በዕለቱ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው እና ሌሎችም የከተማ አሥተዳደሩ መሪዎች ከከተማው ውስጥ የሚከናወኑ ሰው ተኮር የልማት ሥራዎችን ተዘዋውረው እየተመለከቱ ነው።
በከተማ አሥተዳደሩ ውስጥ ጥቅም ሳይሰጡ የቆዩ ቦታዎችን በማልማት የቱሪዝም እና የከተማ ግብርና ምርት ጭምር ግብዓት እንዲኾኑ እየተሠራ ነው።
ይህም ከተረጅነት በመውጣት እመርታዊ ለውጥ ለማምጣት ያስቻለ ስለመኾኑ ተጠቅሷል።
በከተማው ውስጥ በከተማ ግብርና የሚለማ የሩዝ ሰብል፣ የዶሮ እርባታ እና ሌሎችም ልማቶች ምልከታ እየተካሄደ ነው።
ዘጋቢ፦ አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleበሀገር ላይ እምርታዊ ለውጥ ለማምጣት ሁሉም ተማሪዎች ወደ ትምህርት እንዲመለሱ ማድረግ ይገባል።
Next article“ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሀገሪቱ የዲፕሎማሲ አቅም ማሳያ ነው” ሙሉነሽ ደሴ (ዶ.ር)