በባሕር ዳር ከተማ ኤግዚቪሽንና ባዛር ተከፈተ።

6
ባሕር ዳር: ጳጉሜን 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ምግብ ዋስትናና ሴፍትኔት ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት የሴፍትኔት ተጠቃሚዎችን የገበያ ትስስር ለመፍጠር እና የምርት ማስተዋወቅ ሥራን ለማጠናከር የኤግዚቪሽንና ባዛር እያካሄደ ነው።
ዛሬ በተከፈተው የኤግዚቪሽንና ባዛርም ከስልጠናና ምክር እንዲሁም ድጋፍ ባሻገር ዋስትና ወስደው የራሳቸውን የሥራ እንቅስቃሴ የጀመሩ የሴፍትኔት ተጠቃሚዎች ናቸው እየተሳተፉ የሚገኙት።
በኤግዚቪሽንና ባዛሩ የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማውን ጨምሮ የከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት ነው በይፋ የተከፈተው።
በኤግዚቪሽንና ባዛሩ ላይ በከተማ ግብርና የለሙ እለታዊ ፍጆታዎች፣ የእንስሳት ተዋጽኦዎች፣ አልባሳት እና ሌሎችም ምርቶች ቀርበዋል።
ኤግዚቪሽንና ባዛሩ ከጳግሜን 01- 03/2017 ዓ.ም የሚቆይ ይሆናል።
ዘጋቢ፦ ሮዛ የሻነህ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመከልከል የተቋማት ቅንጅታዊ አሠራርን ማጠናከር ይገባል።
Next articleየተደረገው የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ የወላጆችን ጭንቀት ያስወገደ ነው።