የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮ-ሱዳን የባቡር ፕሮጀክት የአዋጭነት ጥናት 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አጸደቀ፡፡

338

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 03/2012 ዓ.ም (አብመድ) የአፍሪካ ልማት ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ለኢትዮ-ሱዳን የባቡር ፕሮጀክት የአዋጭነት ጥናት ለኢትዮጵያ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ድጋፍ አጽድቋል፡፡

1 ሺህ 522 ኪሎ ሜትር የሚረዝመውና አዲስ አበባን ከካርቱም የሚያገኛኘው የባቡር ፕሮጀክት እንዲገነባ በሁለቱ ሀገራት መንግሥታት ይሁኝታን ማግኘቱ ይታወሳል።

የባቡሩ ፕሮጀክቱ ከካርቱም አልፎም በቀይ ባሕር ከሚገኘው ፖርት ሱዳን ጋር የሚገናኝም እንደሆነ ታውቋል።

ባንኩ ያጸደው ድጋፍ ለአዋጭነት ጥናቱ ከሚያስፈልገው 3 ነጥብ 4 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር 35 በመቶውን የሚሸፍን መሆኑን ሎጄስቲክ አፍሪካን ጠቅሶ ፋኮ ዘግቧል።

ለኢትዮ-ሱዳን የባቡር ፕሮጀክት የአዋጭነት ጥናት የሚያስፈልገው ቀሪ ወጪ 2 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር በአፍሪካ ልማት አዲስ አጋርነት (ኔፓድ) የመሠረተ ልማት ፕሮጀክት ዝግጅት ፋሲሊቲ በድጋፍ መልኩ እንደሚሸን ይጠበቃል።
ሁለት ዓመታትን የሚፈጀው የአዋጭነት ጥናት የባቡር ፕሮጀክቱን ቴክኒካዊ፣ ኢኮኖሚያዊ፣ አካባቢያዊ ተስማሚነትን እንዲሁም አማራጭ የፋይንስ ዝግጅትን የሚዳስስ ነው።

ባንኩ ኢትዮጵያ እና ሱዳንን ጨምሮ የአፍሪካ ቀንድን የሚያስተሳስሩ ከፍተኛ አቅም ያላቸው መንገዶች አለመኖራቸው በንግድ፣ ልማት እና ቀጣናዊ ውሕደት ላይ ክፍተት መፍጠሩን ነው የገለፀው።

ተጨማሪ መረጃዎችን
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ዩቱዩብ https://bit.ly/38mpvDC ያገኛሉ፡፡

Previous articleየታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የሦስትዮሽ ድርድር ትናንት ተጀምሯል፤ ዛሬም ቀጥሎ እንደሚውል ታውቋል፡፡
Next articleየእምቦጭ አረምን በዘላቂነት ለማስወገድ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተቀናጀ አሠራር እንደሚያስፈልግ የዩኒቨርሲቲዎች የሥራ ኃላፊዎች ተናገሩ፡፡