“የማኅበሩ ዓላማ የወጣቶችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው”

5
ባሕር ዳር: ጳጉሜን 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ወጣቶች ማኅበር ”የተደራጁ ወጣቶች የሰላም እና የልማት አቅም ናቸው” በሚል መሪ መልዕክት 6ኛ መደበኛ ጉባኤውን በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ነው።
የአማራ ወጣቶች ማኅበር ሊቀመንበር ዓባይነህ ጌጡ ማኅበሩ በ1995 ዓ.ም መመሥረቱን ገልጿል፡፡
የማኅበሩ ዓላማም የወጣቶችን ምጣኔ ሃብታዊ እና ማኅበራዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ነው ብሏል። ባለፉት 22 ዓመታትም በርካታ ሥራዎች እንደተሠሩ ተናግሯል።
በተለይ ደግሞ ባለፉት አምስት ዓመታት በተለያዩ ችግሮች ውስጥ ኾኖ ማኅበረሰቡ ላይ የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት ጥረት ሲያደርግ መቆየቱን ነው የገለጸው።
የዛሬው 6ኛ መደበኛ ጉባኤውም መሥራት የሚችሉ ወጣቶች ወደፊት እንዲመጡ ዕድል የሚፈጠርበት እንደኾነ ገልጿል።
በመድረኩ የሚመለከታቸው የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እና ከክልሉ የተውጣጡ ወጣቶች እየተሳተፉ ነው።
ዘጋቢ፦ ፍሬሕይወት አዘዘው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleለሀገራችን ሁለንተናዊ ሰላም በጽናት ዘብ እንቆማለን።
Next articleየሕዳሴ ግድብ ምረቃ ዋዜማ ላይ ኾነን “የጽናት ቀንን” ማክበራችን ልዩ ትርጉም የሚሰጠው ነው።