
ደሴ: ጳጉሜን 1/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የጽናት ቀን ”ጽኑ መሠረት ብርቱ ሀገር” በሚል መሪ መልዕክት በኮምቦልቻ ከተማ እየተከበረ ነው።
በሀገር አቀፍ ደረጃ “የጽናት ቀን” ኾኖ የተሰየመው ጳጉሜን 1/2017 ዓ.ም በከተማዋ ሲከበር የፖሊስ፣ የሚሊሻ እና የፌዴራል ፖሊሶች የሰልፍ ትርዒት አቅርበዋል።
ከአሚኮ ጋር ቆይታ ያደረጉት የጸጥታ አባላት እና መሪዎች የጽናት ቀንን ሲያከብሩ አባቶቻቸው ታግለው ያስረከቧቸውን ነፃ ሀገር በማሰብ በጽናት እና በአንድነት በመቆም እንደኾነ ተናግረዋል።
የዕለቱ የሰልፍ መርሐግብርም የኢትዮጵያ ብሔራዊ መዝሙርን በመዘመር እና ለሠንደቅ ዓላማው ክብር በመስጠት ተጠናቅቋል።
ዘጋቢ፦ ደምስ አረጋ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን