የጽናት ቀን በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ጽሕፈት ቤት ተከበረ።

1
አዲስ አበባ: ጳጉሜ 01/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በሀገር አቀፍ ደረጃ የጽናት ቀን ኾኖ የተሰየመው የ2017 ዓ.ም ጳጉሜ 1 ቀን የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኀላፊ ሊዲያ ግርማ በተገኙበት ታስቧል።
ዕለቱ በመከላከያ ሠራዊት፤ በፌዴራል ፖሊስ እና በማርሽ ባንድ ታጅቦ ነው የተከበረው። ዕለቱም የኢትዮጵያን ሕዝብ መዝሙር በመዘመር እና ለሰንደቅ ዓላማ ክብር በመስጠት ተጠናቋል።
ዘጋቢ፦ በለጠ ታረቀኝ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“በሁሉም ዘርፎች በምናደርገው ተጋድሎ የኢትዮጵያን መሠረት እናጸናለን” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)
Next articleየአሸናፊነት ትልቁ ምስጢር ጽናት ነው።