በ171 የምዝገባ ጣቢያዎች የምዝገባ ሥራውን ዲጂታላይዝድ ማድረግ ተችሏል።

2
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ‎የአማራ ክልል ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ ትውውቅ ዙሪያ ከዞን ቡድን መሪዎች እና ከሚመለከታቸው አካላት ጋር እየተወያየ ነው።
‎በመድረኩ መልእክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ሲቪልና ቤተሰብ ምዝገባ አገልግሎት ኀላፊ መዓዛ በዛብህ በ2017 በጀት ዓመት በዋናነት ቴክኖሎጂን ተደራሽ የማድረግ፣ የመልካም አሥተዳደር እና የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ትኩረት ተሰጥቶ መሠራቱን ገልጸዋል።
‎የቴክኖሎጅ ዘርፉን ለማበልጸግ መሠራቱንም ተናግረዋል። ቀደም ሲል በባሕር ዳር ከተማ ብቻ የነበረውን በክልሉ አምስት ሪጂኦ ፖሊታንት ከተሞችን በመጨመር በስድስት ከተሞች በ171 የምዝገባ ጣቢያዎች የምዝገባ ሥራውን ዲጂታላይዝድ ማድረግ ተችሏል ብለዋል።
በእነዚህ ከተሞች ብቻ ከ63 ሺህ በላይ ሁነቶች መመዝገቡንም ገልጸዋል። በዚህም ሥራ ከ2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ ለሕትመት የሚወጣ የመንግሥት ገንዘብ ማዳን ተችሏል ነው ያሉት።
‎ዘጋቢ፦ ፍሬሕይወት አዘዘው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous article“በበጎ ፈቃድ አገልግሎት ተግባራት ተስፋ ሰጪ ውጤቶችን አይተናል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next article“ወጣቶች ለአየር ንብረት ለውጥ የማትበገር አፍሪካን የሚገነቡ መሐንዲሶች ናቸው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ