ኀብረት ሥራ ማኀበራት ገበያን በማረጋጋት ረገድ ሚናቸው ከፍተኛ ነው።

2
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ኀብረት ሥራ ኮሚሽን የ2017 ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2018 ዓመት ዕቅድ ትውውቅ መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እያካሄደ ይገኛል።
ኀብረት ሥራ ማኀበራት ገበያን በማረጋጋት፣ የአርሶ አደሮችን ምርት ከገበያ ጋር በማስተሳሰር እና የሥራ ዕድል በመፍጠር ረገድ ሚናቸው ከፍተኛ መኾኑን የኮሚሽኑ ዋና ኀላፊ ጌትነት አማረ ተናግረዋል። በተለይ አሁን ላይ ለሀገር እድገት ያላቸው አበርክቶ ጉልህ መኾኑን ነው አቶ ጌትነት የገለጹት።
በውይይቱ ላይ የክልል፣ የዞን እና የወረዳ ከፍተኛ መሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፦ በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleየኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ በባሕር ዳር አውደ ጥናት እያካሄደ ነው።
Next articleየኢትዮጵያ ማንሰራራት ብስራት የኪነጥበብ ጉዞ ወደ ሩሲያ ሊደረግ ነው።