የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ በባሕር ዳር አውደ ጥናት እያካሄደ ነው።

4
ባሕር ዳር: ነሐሴ 30/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ 113 ከተሞችን በአባልነት የያዘው የኢትዮጵያ ከተሞች የትብብር መድረክ በባሕር ዳር አውደ ጥናት እያካሄደ ነው።
በመድረኩ በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የከተማ ዘርፍ አሥተባባሪ እና የከተማና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አህመዲን መሐመድ(ዶ.ር)ን ጨምሮ ሌሎችም የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
በትብብር መድረኩ የአማራ ክልል ከተሞች ከንቲባዎች፣ የከተማ ሥራ አሥኪያጆች እና የሚመለከታቸው መሪዎች እየተሳተፉ ነው።
በክልሉ የሚገኙትን ከተሞች በትብብር መድረኩ አባልነት በማሣተፍ በከተማ ልማት ዘርፎች በትብብር አብሮ ለመሥራት የሚያስችል ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።
ዘጋቢ: አሰፋ ልጥገበው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleበጸጥታ ምክኒያት አቋርጠው የነበሩ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እየተመለሱ ነው።
Next articleኀብረት ሥራ ማኀበራት ገበያን በማረጋጋት ረገድ ሚናቸው ከፍተኛ ነው።