
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሥራና ሥልጠና ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት እቅድ ትውውቅ እያካሄደ ነው።
የአማራ ክልል ሥራና ሥልጠና ቢሮ ኀላፊ ስቡህ ገበያው (ዶ.ር) ባለፉት ዓመታት ክልሉ ችግር ውስጥ ቢኾንም ዓበይት ሥራዎች መሠራታቸውን ጠቅሰዋል።
በ2017 በጀት ዓመትም ካለፉት ዓመታት ለየት ያሉ ሥራዎች መሠራታቸውን ተናግረዋል። በበጀት ዓመቱም ለ1 ነጥብ 3 ሚሊዮን ወጣቶች የሀገር ውስጥ እና የውጭ የሥራ እድል ተፈጥሯል ብለዋል።
ከዚህ መካከል በቢሮው በለሙ ሰባት ሲስተሞችም 300 ሺህ ገደማ ለሚኾኑ ሥራ ፈላጊዎች ሥራ መፈጠሩ ዓመቱን ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
ከዞን፣ ከከተማ አሥተዳደር የሥራ መሪዎች እና በክልሉ ከሚገኙ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ዲኖች ጋር የዓባይ የቃል ኪዳን ፊርማ ሥነ ሥርዓት ተካሂዷል።
የዓባይ ቃል ኪዳን የፊርማ ሥነ- ሥርዓት የዓባይ ግድብ የሚጠናቀቅበት ወቅት በመኾኑ የሥራና ክህሎት የቀጣይ ተግባራትን እንደዓባይ ግድብ በውጤታማነት ለመፈጸም የተደረገ ስምምነት መኾኑ በመድረኩ ተመላክቷል።
ዘጋቢ:- ሮዛ የሻነህ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን