
ደብረ ማርቆስ፡ ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) 1 ሺህ 500ኛው የመውሊድ በዓል በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር እየተከበረ ይገኛል።
የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የልደት በዓል በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር በታላቁ ቢን አፊፊ መስጅድ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሁነቶች ነው እየተከበረ የሚገኘው።
የደብረ ማርቆስ ከተማ ታላቁ ቢን አፊፊ መስጅድ ኢማም ሼህ መሐመድ ሽፋው ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ለሰው ልጆች ፍቅርን፣ መከባበርን፣ አብሮ መኖርን ብሎም መተሳሰብን በተግባር ያስተማሩ በመኾናቸው በዓሉ እንደሚከበር ተናግረዋል።
ሙስሊሙ ማኅበረሰብም የመወሊድ በዓልን ሲያከብር የነብዩ አስተምሮዎችን በመፈፀም እንደኾነም ነው ያስረዱት።
የምሥራቅ ጎጃም ዞን ሸሪያ ፍርድ ቤጽ ዳኛ ሼህ ወለላው ሰይድ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የመውሊድ በዓልን ሲያከብር ለሀገር ሰላም እና አንድነት በመፀለይ ብሎም የነብዩን አስተምህሮዎች በተግባር በመግለጽ ሊኾን እንደሚገባ ነው የተናገሩት።
አሚኮ በዓሉን ሲያከብሩ ያገኛቸው የሃይማኖቱ ተከታዮችም በዓሉን በጋራ ማዕድ በመጋራት እያከበሩት እንደኾነ ገልጸዋል።
ቀኑን ነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ)ን በማሰብ እና የእሳቸውን ትዕዛዛት በመፈፀም እያከበሩ እንደሚውሉ ነው የተናገሩት።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን