ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚን መገንባት ይገባል።

5
ባሕር ዳር: ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል አካባቢና ደን ጥበቃ ባለሥልጣን የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት ትውውቅ መድረክ አካሂዷል።
የአካባቢ ደንና አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ኀላፊ ተስፋሁን ዓለምነህ እንዳሉት ክልሉ በችግር ውስጥ ኾኖም በአካባቢ ጥበቃ የተሻለ ሥራ ሲሠራ ቆይቷል።
አካባቢ ጥበቃ ዓለም አቀፋዊ በመኾኑ ለሰው ልጆች መኖሪያ ምቹ እና ጽዱ አካባቢን ለመፍጠር ድርሻው የጎላ ነው ብለዋል። የአማራ ክልልም የአካባቢ ጥበቃ ተግባራትን በትኩረት እየሠራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።
በቀጣይ ይህንን ተግባራት አጠናክሮ በማስቀጠል የብዝኀ ሕይወት ሀብቶችን መጠበቅ እና ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር አረንጓዴ ኢኮኖሚን መገንባት ይገባልም ብለዋል።
በመድረኩ የባለሥልጣኑ ከፍተኛ መሪዎች፣ የከተማ፣ የዞን፣ የብሔራዊ ፓርኮች እና ጥብቅ ሥፍራዎች የሥራ ኀላፊዎች እና ባለሙያዎች ተገኝተውበታል። በመድረኩ የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸመም እና የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ ትውውቅ ሪፖርት ቀርቧል።
በማጠቃለያው በበጀት ዓመቱ የላቀ አፈፃፀም ላመጡ ተቋማት የእውቅና ሽልማት ይሰጣል ተብሏል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleየመንግሥትን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ እና በጠዳ የሥልጠና ማዕከል የቆዩ ታጣቂዎች ሥልጠናቸውን አጠናቀቁ።
Next articleየመወሊድ በዓል ሲከበር ለሀገር ሰላም እና አንድነት በመፀለይ ሊኾን ይገባል።