የመውሊድ በዓል ሲከበር በአብሮነት፣ የተቸገሩትን በማገዝ እና በመረዳዳት ሊኾን ይገባል።

1
ጎንደር፡ ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) ‎‎1ሺህ 500ኛው የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) የመውሊድ በዓል በጎንደር ከተማ ተከብሯል።
‎በበዓሉ የሃይማኖት አባቶች፣ ምዕመናን እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
‎በበዓሉ ተገኝተዉ መልዕክት ያስተላለፉት የጎንደር ከተማ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ሊቀ መንበር ሐጅ አንዋር ቃሲም የዘንድሮው የመውሊድ በዓል የሚከበረው ባለፈው ወር የተካሔደውን የመጅሊስ ሥራ አሥፈጻሚዎች ምርጫ በተሻለ እና ዴሞክራሲያዊ በኾነ መንገድ በተጠናቀቀበት ጊዜ በመኾኑ በዓሉን ልዩ ያደርገዋል ብለዋል።
‎በዓሉን ለሚያከብሩት ኹሉ በመጭው ጊዜ ለአብሮነት ተግተው የሚሠሩበት፣ ጠንክረው ጸሎት የሚያደርጉበት እና ለሀገር ሰላም መከበር የሚሠሩበት እንዲኾንም አመላክተዋል።
‎የጎንደር ዑለማ ምክር ቤት ሠብሣቢ ሼህ ኢብራሒም ሙሐመድ የነብዩ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ስለሰላም፣ አብሮነት እና አንድነት አጥብቀው አስተምረዋል ብለዋል።
‎የመውሊድ በዓል ሲከበርም ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በአብሮነት፣ የተቸገሩትን በማገዝ እና በመረዳዳት ሊኾን እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል።
‎‎በዓሉን ሲያከብሩ አሚኮ ያገኛቸው የሃይማኖቱ ተከታዮች ሀሰን ደሴ እና መከር አልምስጦፋ የመውሊድ በዓልን በመረዳዳት እና በመተጋገዝ እያከበሩት መኾኑን ተናግረዋል።
‎በዓሉም የሰላም፣ የፍቅር እና የአንድነት እንዲኾንም መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ዘጋቢ :- አዲስ ዓለማየሁ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleበ2018 በጀት ዓመት ወደ ፕሮጀክት በጀት ሽግግር እንደሚደረግ ገንዘብ ቢሮ አስታወቀ።
Next article“በምርት ዘመኑ ምርታማነትን በሄክታር 35 ኩንታል ለማድረስ እየተሠራ ይገኛል” ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)