ባለፈው ዓመት በክልሉ በቱሪዝም ዘርፍ አበረታች ውጤቶች ተገኝተዋል።

1
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት የዕቅድ ትውውቅ መርሐ ግብር እያካሄደ ነው።
የአማራ ክልል ባሕል እና ቱሪዝም ቢሮ ኀላፊ መልካሙ ፀጋየ የ2017 በጀት ዓመት ብዙ መሰናክሎች የታለፉበት ዓመት ነው ብለዋል። ኀላፊው ችግሩን ለመሻገር ጠንካራ ሥራ መሠራቱንም ነው የጠቆሙት።
የተጠናቀቀው በጀት ዓመት በርካታ ተግባራት የተከናወኑበት እና ብዙ ዕውቅናዎች የተገኙበት የስኬት ዓመት እንደነበርም ገልጸዋል።
አማራ ክልል በቱሪዝም መዳረሻነቱ ድንቅ ምድር እንደኾነም ቢሮ ኀላፊው አብራርተዋል።
አማራ ክልል እልፍ ፀጋዎች እና የሚዳሰሱ እና የማይዳሰሱ የቱሪዝም መዳረሻዎች ያሉት ክልል መኾኑን ያብራሩት ኀላፊው ይሄን ሀብት በመጠቀም በኩል በትኩረት መሥራት እንደሚገባ አብራርተዋል። ቢሮው ዓመታዊ የእቅድ አፈጻጸምና እቅድ ትውውቅ መድረኩን ማካሄድ እንደቀጠለ ነው።
ዘጋቢ:- ሰመሀል ፍስሀ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን
Previous articleየአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የ25 ዓመቱን ስትራቴጂክ ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ መዘጋጀቱን አስታወቀ።
Next articleበ2018 በጀት ዓመት ወደ ፕሮጀክት በጀት ሽግግር እንደሚደረግ ገንዘብ ቢሮ አስታወቀ።