
ባሕር ዳር: ነሐሴ 29/2017 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል የመንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ የ2017 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ ትውውቅ መድረክ እያካሄደ ነው።
በመድረኩ የተገኙት የቢሮው ኀላፊ መንገሻ ፈንታው (ዶ.ር) ባስተላለፉት መልእክት ዛሬ የምናካሂደው የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ግምገማ እና የ2018 በጀት ዓመት የእቅድ ትውውቅ የክልሉ የ25 ዓመታት እቅድ ትግበራ በተጀመረበት ወቅት ነው ብለዋል።
የኮሙኒኬሽን ቢሮ ከ25 ዓመቱ አሻጋሪ እቅድ የተቀዳ የ2018 በጀት ዓመት አቅዷል ነው ያሉት። በእቅዱ ዙሪያ ተወያይተን እና ካለፉት ችግሮቻችን ተምረን የ2018 በጀት ዓመት እቅድን ለማሳካት ርብርብ ማድረግ እንደሚጠበቅ አንስተዋል።
እንደ ሕዝብ ከገጠመን የሰላም እጦት ለመውጣት በተደረገው ሁለንተናዊ እርብርብ የሚዲያ እና ኮሙኒኬሽን ዘርፉ የድርሻውን ተወጥቷል ያሉት ቢሮ ኀላፊው በቀጣይም የበለጠ በማጠናከር እስከ ታች ድረስ ባለው መዋቅራችን ሁሉንም የሚዲያ አማራጮቾ ተጠቅመን በትጋት መሥራት ይኖርብናል ብለዋል።
የ2018 በጀት ዓመት እቅዳችንን እንደ አንድ ልብ አሳቢ እና እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ኾነን ሙሉ በሙሉ ለማሳካት መዘጋጀት ይኖርብናል ነው ያሉት።
በመድረኩ የቢሮው ኀላፊዎች፣ ዳይሬክተሮች፣ የሚዲያ መሪዎች፣ የዞን እና የከተማ አስተዳደር የኮሙኒኬሽን አመራሮች እና የቢሮው ሰራተኞች መገኘታቸውን ከቢሮው ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!